የምክር ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች
ራዕይ
በሕገ መንግሥቱ ለተረጋገጠው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እኩልነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ዲሞክራሲያዊ አንድነት ዘብ የቆመ ምክር ቤት ሆኖ ማየት፣
ተልዕኮ
ሕገ-መንግስቱን በመተርጎም፣ የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ውሳኔ በመስጠት፣ ፍትሃዊ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በመወሰን፣ ሊፈጠሩ ለሚችሉ ግጭቶችንና አለመግባባቶች ውሳኔ በመስጠት፣ በየሰመረ የመንግሥታት ግንኙነት በማዳበር፣ በሕ/ተ/ም/ቤት ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሃ ብሔር ጉዳዮችን በመለየት፣ ንቃተ ሕገ-መንግሥት እንዲፈጠር በማድረግ፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ግንኙነትን በማጠናከር ዴሞክራሲያዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ማድረግ፣
ዕሴቶች
ሀ/ ሕገ መንግሥታዊነት፣
ለ/ ዴሞክራሲያዊነት፣
ሐ/ ፍትሃዊነት እና/ወይም እኩልነት፣
መ/ ተዓማኒነት፣
ሠ/ አሳታፊነት፣
ረ/ አጋርነት፣
ሰ/ ግልጸኝነት፣
ሸ/ ወቅታዊ ምላሽ፣
አድራሻ
ስልክ ቁ: +251-111-242-301/3
ስልክ ቁ: +251-111-242-309
ስልክ ቁ: +251-111-223-322
ፋክስ: +251-111-242-304/8
ፋክስ: +251-111-241-208
የፖ.ሣ. ቁጥር: 20212/1000
አዲስ አበባ፣ ኢትዮዽያ
የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አመሠራረት፣ ተግባር እና ኃላፊነት
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በኢፌዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 61 የተመሠረተ፣ በአገራችን ክልሎች የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውክልና የሚረጋገጥበት የፌዴራል ምክር ቤት ነው፡፡ በዚህ ምክር ቤት እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ ቢያንስ በአንድ ተወካይ የሚወከል ሲሆን ለያንዳንዱ አንድ ሚሊየን ሕዝብ ተጨማሪ አንድ ወኪል ይኖረዋል፡፡ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት በክልል ምክር ቤቶች አማካይነት ነው፡፡ ምርጫው በቀጥታ አሊያም ደግሞ በተዘዋዋሪ ሊካሄድ ይችላል፤ ይህም ማለት የክልል ምክር ቤቶች አባላቱን በራሳቸው ወይም በቀጥታ በሚደረግ ሕዝባዊ ምርጫ እንዲመረጡ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ በ5ኛው የምክር ቤት ዘመን፣ ምክር ቤቱ በአጠቃላይ 153 አባላት የነበሩት ሲሆን 76 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችም ተወክለዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ታሪክ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተመሠረተው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በጸደቀበት 1987 ዓ.ም. ነው፡፡ ምክር ቤቱ ከተመሠረተ ጀምሮ አምስተኛ የምክር ቤት ዘመን በማገባደድ ላይ ነው፡፡ በምክር ቤቱ ባለፉት አምስት የምክር ቤት ዘመን የሥራ ዓመታት የነበረው የአባላት ውክልና በየጊዜው እያደገ እና እየሰፋ መጥቷል፡፡ በመጀመሪያው የምክር ቤት ዘመን (ከ1987 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም.) 108 አባላት የነበሩት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ1993 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም.)የአባላቱ ቁጥር ወደ 112 ያደገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሴቶች ብዛት 8 ሆኖ ነበር፡፡ በሦስተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ1998 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም.)የምክር ቤቱ አባላት ብዛት 121 ሲደርስየሴቶች ቁጥርም 22 ደርሷል፡፡ በአራተኛው የምክር ቤት ዘመን (ከ2003 ዓ.ም.እስከ 2007 ዓ.ም.) የምክር ቤቱ አባላት 135 ሲሆን...