የፌዴራል መሠረተልማት ክልላዊ ሥርጭት ፍትሐዊነትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ
ዓርብ ሰኔ 05/2012 ዓ.ም. የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል መሠረተልማት ክልላዊ ሥርጭትና ፍትሐዊነትን በተመለከተ በሥርጭት መስፈርቶች ላይ እና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል አፈጻጸም የክትትልና ቁጥጥር አስመልክቶ ከፌዴራል መሠረተልማት ተቋማት እና የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፣ የፌዴራል መስኖ ልማት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት፣ የሳይንስና ከፍተኛ ት/ት ሚ/ር ከፍተኛ ተቋማት የኢትዮ-ቴሌኮም እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ሥርጭት ፍትሃዊነት መስፈርቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ጠቃሚ ሃሳቦችና አስተያየቶችም ተሰጥቶባቸዋል፡፡