አገራዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ሪፖርት ቀረበ

የውይይቱ መነሻም ከዚህ ቀደም በተደረገው ሪፖርትና የውይይት መድረክ የታዩትን ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ እነዚህ ክፍተቶች ተስተካክሎ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሠረተ ሪፖርት እንዲቀርብ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ነው፡፡

ሪፖርቱ ያካተታቸው ዋና ዋና መሠረተልማት አውታሮች ስምንት ሲሆን እነሱም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣የኢትዮ ቴሌኮም፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቌም፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፣የኢትዮጱያ ኤርፖርቶች፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣የመስኖ ልማት ኮሚሽንና ኢንዱስትሪያል ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን ይገኙበታል፡፡ በውይይቱ ስለፍትሐዊነትና ስለመሰረተ ልማቶች መሥፈርቶች ጥያቄ ተነስቶባቸው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ፍትሐዊነትን ፣የዜጐችን ተጠቃሚነትንና አዋጭነትን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ በሚገባ እንዲታዩ ተጠቁመዋል፡፡ በአብዛኛው በሁሉም መስኮች የበጀት እጥርት መሆኑ ተነስቷል፡፡

በመጨረሻም ተቌማቱ ከክልሎች ጋር የተሳለጠ ውይይት ማካሔድ እንደሚጠበቅባቸው ፣የአሥር ዓመት መሪ እቅድ ክፍተቶችን በሚያሟላ መልኩ አዋጭነቱን ታሳቢ በማድረግ፣ የልማቱን ቀጣይነት በሚያረጋግጥ ሁኔት እንዲዘጋጅ፣ ተቌማቱ የሚያስቀምጡ መሥፈርቶች ከሌሎች ጋር ተነባቢነት ባለው መልኩ ከበጀት አቅም የተገናዘበ( የበጀት ምንጭ) በግልፅ በሚያሳይ ሁኔታ፣ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ግልጽና ከሕዝቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኮሙኒኬሽን ሥራ እንዲሰራ ለሌላ ዓላማ ፍጆታ በማይውል አግባብ እንዲሆን በየክልሉ የመሰረተ ልማት ደህንነት ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠውና በየአስተዳደር እርከኑ ያሉ ኃላፊዎችና የልማቱ ባለቤት የሆነው ሕዝብ ኃላፊነት እንዲወስዱ ማብቃት የሚሉ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና አሁንም የፍትሃዊነት ችግሮች እንዳሉ በማስመልከት በሂደት እንዲስተካከል በመጠቆም ውይይቱ አብቅቷል፡፡