የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔሮችና ህዝቦ ቀን በዓል/ የህገ መንግስት ቀን/ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች

የኢ.... የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሦስተኛው የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት የሥራ ጊዜ ሚያዝያ 21/1998 . ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰብዓዎና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ዋስትና የሆነው የኢ.... ሕገ መንግስት የፀደቀበትን ህዳር 29 ቀንየኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን”/የህገ መንስት ቀን/ ሆኖ በየዓመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እንዲከበር ወስኗል፡፡

በዚህ የምክር ቤቱ ውሳኔ መሠረት እለቱ በበዓልነት ከህዳር 29/1999 . ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች አስተናጋጅነት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በልዩ ልዩ ዝግጅቶችና ልማታዊ ፍፃሚዎችና ክንዋኔዎች ላለፉት አስራ ሁለት ጊዜያት በድምቀት ተከብሯል፡፡

አስራ ሦስተኛው በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት 2011 . ህዳር 29 ቀን ለማክበር በብሔራዊ ደረጃ የበዓሉ መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ውይይት ተደርጎበት ከፀደቀ በኋላ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ የአስተናጋጁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዕቅድም ከበዓሉ መሪ እቅድ ጋር በመናበብ የዝግጅት ምዕራፍ ተበናቆ ወደተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡

በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች አስተናጋጅነት እስከ አሁን ለአስራ ሁለት ዓመታት ያከበርነው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የታለመውን ዓላማ ከማሳካት እንፃር ያስገኘው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

በበዓሉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማመላከትና ውስንነቶችን በመለየት የተሸለ ሥራ መስራት እንዲቻልም በበዓሉ ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡ ሁሉንም የአገራችን ክልሎችና አከባቢዎች ትኩረት ባደረገ መልኩ በተካሄደው በዚህ የዳሰሳ ጥናት ትንተና መነሻነት በዓሉ የላቀ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ በማስገኘት ውጤታማ መሆኑን ከአመላካች ግብዓቶች ለማወቅ ተችሏል፡፡

በበዓሉ ምክንያት የሚካሄደው የልማት ሥራዎ በዘላቂነት እንዲያገለግሉ በማድረግ በየደረጃው የሚካሄዱ ሲምፖዚየሞችና ፓናል ውይይቶች የሕገ መንግስት አስተምሀሮና የፌዴራሊዝም ስርፀት በተመለከተ ሰፊ ሥራዎች መሠራት እንደሚያስፈልግ አመላክቷል፡፡

በሕገ መንግስት አስተምህሮና ስርፀት ሲታይ በአንፃዊ መልኩ ሕብረተሰቡ የተሻለ ሕገምንግስታዊ ግንዛቤ እንዲኖረው ጥረት ተደርጓል፡፡ ይሁንና በዚህ ረገድ በበዓሉ ወቅት ብቻ ሳንወሰን ተከታታይነትና ዘላቂነት ባለው አሰራር ሕገ-መንግስታዊ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎችን የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም ሰፊ ሥራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

በዚህ በዓል ምክንያት በሁልም ክልሎች የሚገኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች የእርስ በእርስ ትስስርና ግንኙነትን ዴሞክራሲያዊ አንድነት በማጠናከር ካለፉት ስኬታማ በዓሎቻችን የተገኙትን ልምዶች በማጎልበት ከመቼውም የተሻለ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ የመገንባት ተልዕኮኦች ላይ የህብረተሰቡ ግንዛቤ ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

በዓሉ በአስተናጋጅ ክልሎች መከበሩ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አካባቢዎች የክልልና የከተማ አስተዳደሮችም ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በፌዴራለና በክልል መንግስታዊ መስሪያቤቶች በተለያዩ የግል ድርጅቶች እንደየተዋረዱ በወጣቶችና ሴቶች በአጠቃላይ በሁሉም ዜጎች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት የሚከበር በዓል እየሆነ መጥተዋል፤

በበዓሉ ምክንያት በአስተናጋጅ ክልል የተነሱ የልማት ስራዎች ከሚያስገኙት ጥቅም ጋር የአገራችን ህዝቦች አንድነት የእርስ በእርስ ትስስር በማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው፡፡ በአስተናጋጁ ክልል ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የክልሉን እምቅ ሀብት በመጠቀም ለአገልግሎት ለማዋልም ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

በበዓሉ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያላቸውን አኩሪ ባህል፣ ታሪክና እሴቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት ብዝሃነታችንን ከተጠቀምንበት ውበትና መልካም አጋጣሚ የሚፈጥርና አንዱ በሌላው እውቅና የሚሰጥበትና የመከባበር ስርዓትን በተግባር በመለማመድ ዲሞክራሲያዊ አንድነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዳ ፤የአገራችንን ገፅታ ከመገንባት አንፃር በዓሉ ከዓመት አመት የተሻለ ህዝባዊ ተሳትፎና ሕዝቡንም የልማት ተጠቃሚ በማድረግ፤

የአገራችን // እርስ በእስሳቸው የበለጠ እንዲተዋወቁ ዕድል የሚፈጥርበት ሲሆን እንዱ የሌላውን ማንነት፣ ባህልና ማህበራዊ እሴት በተሸለ መልኩ እንዲገነዘቡ ያስቻለ ነው፡፡

በተለይም የጋር እሴቶቻችንን ከማዳበርና ከማጠናከር የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል በዓሉ ህዝባዊ መነሳሳት በመፍጠር ለቀጣይ ልማት መነቃቃት የሚፈጥር ነው፡፡

በሌላ በኩል አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ ከመገንባት አንፃር በዓሉን ምክንያት በማድረግ በልማት ኤግዚቢሽን በንግድ ትርዒትና ባዛር ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ በጥቃቅንና አንስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባላቸው ተሳትፎ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ የገበያ ትስስር በመፍጠር የላቀ ፋይዳ የሚያስገኝ ነው፡፡