Committee
Democratic Unity Standing Committee
-
በሕዝቦች እኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተአንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር የሚያስችል አገራዊ አመለካከት እንዲፈጠር የሚያስችሉ ተግባራትን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡
-
በክልሎቸ እንዲሁም በክልልና በፌደራል መንግስት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን አስመልክቶ ከምክር ቤቱ የሚመሩለትን ጉዳዮች መርምሮ በሕ-ገመንግስቱና በሌሎች ሕጎች በተደነገገው መሰረት የውሳኔ ሀሳብ ለምክርቤቱ ያቀርባል፡፡
-
ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ የፍትሃብሔር ጉዳዮች በጥናት እንዲለዩ በማድረግ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡
-
የሕብረተሰቡን ንቃ-ሕገመንግስት ለማዳበር የሚያስችሉ ስልቶች እነዲቀየሱና የሕገ-መንግስት አስተምህሮ በተለያዩ ዙሪያዎች እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡
-
ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የጣሉ ወይም ሊጥሉ የሚችሉ ጉዳዮች ሊኖሩ በራሱ ተነሳሽነት ወይም በሚመለከታቸው አካላት ሊቀርብለት መርምሮ በጥናት ላይ በመመስረት የችግሮቹን መንስኤዎችና መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡
-
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ አከላለልን አስመልክቶ ለምክርቤቱ የሚያቀርበውን ረቂቅ መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡
-
ለተሰጠው ስልጣንና ተግባር አፈፃፀም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች የሚሰበስቡበትንና ጥናቶች የሚያካሂዱበትን ስልት እንዲቀየስ ያደርጋል፡፡ በስራላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
-
በምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡